yJ9i21554672343

ክፍል 1

የመርከብ ንግድና የባህረኞች ስራ በባህሪው አለም አቀፋዊ ነው። መርከብ ላይ የሚሰሩ ባህረኞችም በአብዛኛው ግዜ በስራ ላይ የሚቆዩት ከሚኖሩበት ሃገርና ከሚያሰራቸው ካምፓኒ ቢሮ ርቀው ነው። መርከብ ላይ የሚቀጥሩዋቸውም ወይም አሰሪዎቻቸው ዋና ቢሮዋቸው አንድ ሃገር ሲሆን፤ መርከቧ የተመዘገበችው ደግሞ ሌላ ሃገር ነው። በተለይ አሁን ባለው የመርከብ አሰራር ለምሳሌ መርከቧ የተመዘገበችው ፓናማ ሃገር ፤ የመርከቧ ባለቤት ከጀርመን፤ መርከቧን የተከራየው ከሲንጋፖር፤ መርከቧን የሚያስተዳድረው ከህንድ፤ ባህረኞቹ ደግሞ ከተለያየ ሃገር የተውጣጡ አይነት አሰራር የተለመደ ነው። ትልቁ ጥያቄ ባህረኞቹን በተመለከተ ሃላፊነት የሚወስደው ማን ነው? ወይም በየትኛው ሃገር ህግ ነው የሚዳኘው? በዚህና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች የተነሳ ቀደም ባሉት ዘመናት ባህረኞች የተለያየ በደልና መጉላላት ሲደርስባቸው ነበር።

የተለያዩ ሃገራት የባህረኞችን የድህንነትና የጤና ሁኔታ ለመንከባከብ የሚያስችሉ ህግና ደንብ ቢያወጡም በተቃራኒው ደግሞ አንዳንድ ሃገራት ምንም ህግና ደንብ ስራ ላይ አላዋሉም። በተጨማሪም International Maritime Convention (MLC) በአለም አቀፍ ደረጃ በ 2013 ከመጽደቁ በፊት የነበሩት የ International Labour Organization (ILO) conventions ወጥነት የጎደላቸውና በአብዛኛው የወቅቱን የባህረኛ መብት ማስከበር አልቻሉም። እነዚህ ቆየት ያሉ ኮንቨንሽኖችን ሃገራት በፈለጉት መንገድ መርጠው የመተግበር አዝማሚያ ስለነበር በጣም ውስብስብ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። የባህረኞች ደህንነት ከምን ግዜውም በበለጠ በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረትን ስለሳበ አዲስ ጠቅለል ያለ፤ ለመተግበር የማያስቸግርና ሁሉንም ሃገራት በእኩልነት የሚያስተሳስር ህግ ማውጣት አስፈላጊ ነበር። አዲሱ International Maritime Convention (ከዚህ በኋላ MLC ብለን እንጠራዋለን) ከዚህ በፊት የነበሩትን ወደ 68 የሚጠጉ ILO conventions በአንድነት ተጠቃሎ ለመተግበር በሚመች መንገድ ቀርቧል።

 

በ2013 በአውሮፓውያን አቆጣጠር በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኘው MLC ሁለት መሰረታዊ አላማዎች አሉት።

 1. የመጀመርያው የባህረኞችን የስራና የአኗኗር መብት በአለም አቀፍ ደረጃ ወጥነት እንዲኖረው ማድረግና
 2. ሁሉም የመርከብ ባለቤቶችና አለም መንግስታት በእኩልነት ግዴታቸውን እንዲወጡና ለባህረኞች የሚገባውን እንክብካቤ እንዲያረጉ፤ ይህን የማያደርጉ ከሚጠበቅው ደረጃ ውጭ ያሉ የመርከብ ባለቤቶችም ሆኑ ሃገራት በተቀመጠው አለም አቀፍ አሰራር መሰረት ለቅጣት የሚዳረጉበትን መንገድ እንዲኖር ማድረግ ነው።

   MLC አለም አቀፋዊ ተግባራዊነት ሲኖረው፤ ከበፊቶቹ የ ILO conventions በተሻለ ሁኔታ በቀላሉ ለመረዳት እንዲቻል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪም ሃገራት በተወሰነ መንገድ በአፈጻጸሙ ላይ ምርጫ እንዲኖራቸው ተደርጎ የተዘጋጀ ቢሆንም ሁሉም ሃገራት ግን ወጥነት ባለው መንገድ እንዲተገብሩት ተደርጎ በቀላሉ የተዘጋጀ ኮንቬንሽን ነው።

ይህ በ ILO የረቀቀው በአለማችን ላይ እስከ አሁን ለባህረኞች መብት መከበር በቀዳሚነት የሚነሳ ኮንቬንሽን በማሪታይም ዘርፍ ‘አራተኛው ምሰሶ’ በመባል ይታወቃል። ሌሎቹ ሶስቱ ምሰሶዎች፤ The Safety of Life at Sea (SOLAS), Standards of Training, Certification and Watchkeeping (STCW) and Prevention of Pollution from Ships (MARPOL) ናቸው።

 

            ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ፡ በሚያስገርም ሁኔታ የሰራተኞችን መብት ለማስከበር ኢትዮጵያ የ ILO አባል የሆነችው በ1923 በአውሮፓውያን አቆጣጠር ነው። ከዛም በኋላ በተለያዩ ግዜያት 22 የሚሆኑ የ ILO conventions ፈርማለች። ምንም እንኳን አብዛኛው በየብስ ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች ታስቦ የተፈረመና ወደ ሃገራችን ህግ የተቀየረ ቢሆንም፤ ባህረኞችም በተወሰነ መልኩ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ህጎች ተግባር ላይ ውለው ነበር። ስለሃገራችን ባህረኞችን በተመለከተ አሁን በተጨባጭ ያለውን ነገር ወደፊት በሰፊው የምንዳስሰው ይሆናል። ለ አሁን ግን በአለም አቅፍ ደረጃ ስለ MLC ና ባህረኞች ስለ መብታቸው ማወቅ የሚገባቸውን ነገር አንኳር የሆኑትን እያነሳን አንድ ባንድ እናያለን።

MLC ይዘት

ኮንቬንሽኑ ሶስት የተለያዩ ነገር ግን የሚያያዙ ክፍሎች አሉት፤ the Articles, the Regulations and the Code። The Articles and Regulations ዋና ተብለው የተለዩትን መብትና መርሆችን እንዲሁም ኮንቬንሽኑን የፈረሙ አባል ሃገራት ያለባቸውን ግዴታዎች በዝርዝር ይዟል። The Code የሚባለው ሶስተኛው ክፍል በሁለተኛው ክፍል የተዘረዘሩትን ህጎች እንዴት መተግበር እንዳለባቸው ይዘረዝራል። The Code በተጨማሪ በሁለት ንዑስ ክፍሎች Part A (mandatory Standards) እና Part B (non-mandatory Guidelines) ተብሎ ተከፍሏል።

 

ከዚህ በፊት በነበሩ የ ILO conventions ባልተለመደ መልኩ፤ ለመተግበር ይረዳ ዘንድ ሁለተኛውና ሶስተኛው ክፍሎች (The Regulations እና the Code) በአምስት ርዕሶች ተከፍለዋል፤

 • Title 1: Minimum requirements for seafarers to work on a ship
 • Title 2: Conditions of employment
 • Title 3: Accommodation, recreational facilities, food and catering
 • Title 4: Health protection, medical care, welfare and social security protection
 • Title 5: Compliance and enforcement.

መሰረታዊ መብቶች

በ (MLC) ኮንቬንሽን አባል ሃገራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ የሰራተኞች መብቶችን በህግና ደንቦቻቸው  ማክበር እንዳለባቸው ያስቀምጣል። እነዚህም መሰረታዊ መብቶች፡

 • የመደራጀት መብት፤ የፈለግነው የሰራተኞች ማህበር አባል መሆን
 • በህብረት የመደራደር መብትን እውቅና መስጠት፤ በሰራተኛ ማህበራት አማካኝነት የጋራ ድርድር ስምምነትን ማዘጋጀት
 • ማንኛውንም አስገድዶ ማሰራትን ማስወገድ፤ በራስ ፍጹም ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ስራ መስራት፤ በሰራነው መጠን ክፍያ መቀበል
 • ለጋ ልጆችን ስራ ላለማሰራት
 • አድሎና መድሎ የሌለበት የስራ አቀጣጠርና የስራ ሁኔታ፤ ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ ሰዎች ከዘር፤ ሃይማኖት፤ ዜግነት፤ ጾታ ወይም የፖለቲካ አቋም የተነሳ አድሎ ሳይደረግ እኩል የሚታዩበት

ከላይ የተዘረዘሩት መሰረታዊ መብቶች ወደ ባህረኞች ሲመጣ፤ ሁሉም ባህረኛ ጥንቃቄና ደህንነቱ የተረጋገጠ የስራ ቦታ እንዲኖረው፤ ሚዛናዊ የሆነ የስራ አቀጣጠር፤ የተመቻቸ የስራና የመኖርያ ቦታ ማግኘት፤ ማህበረሰባዊ ጥበቃ ለምሳሌ ህክምና እና የጤና እንክብካቤ እንዲሁም ለመዝናኛ የሚያስፈልጉ ነገሮች የማግኘት መብት አለው።

 

አተገባበር

ከላይ የተዘረዘሩት መሰራታዊ መብቶችን ጭምሮ በ(MLC) ኮንቬንሽን የተዘረዘሩት የባህረኞች መብት እንዴት ነው ተግባራዊ የሚሆኑት? ከላይ በመግቢያው ላይ እንደገለጽኩት የመርከብ ስራ አለም አቀፍ ስለሆነ አንድ ህግ ሲወጣ ለመተግበር ያለውም አሰራር የዛን ያህል አስቸጋሪ ነው። ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት የ(MLC) ኮንቬንሽን አተገባበርን መግለጽም ግድ ይላል። በ (MLC) ኮንቬንሽን በራሱ ምንም ጉልበት የለውም። አንድ ሃገር (MLC) ኮንቬንሽን ሲፈርም ወደ ሃገሩ ብሔራዊ ህግ ማስገባት አለበት። ለምሳሌ እትዮጲያ ስትፈርም በሃገሪቷ ህግ ተቀርጾለት በህዝብ ተወካዮች ፀድቆ በነጋሪት ጋዜጣ ሲወጣ ነው የመተግበር ሃይል ያለው። በተጨማሪም በሃገር ደረጃ የተሰጠውን ተፈፃሚነት ለመደገፍ በ ህብረት ስምምነት፤ በ ፈቃደኝነት እንዲሁም በምርመራና በብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የ (MLC) ኮንቬንሽን ተፈፃሚነት ሃይል ያገኛል። እዚህ ጋር ማስተዋል የሚያስፈልገው የ(MLC) አፈጻጸም የ ሶስትዮሽ (ባህረኛው፤ አሰሪውና መንግስት) ተሳትፎ ያለበት መሆኑን ነው። በሃገራችንም የሚታየው ከባህረኞች ጋር የተያያዘ ጥያቄ መልስ የማያገኘው (በተለይ ከ EMTI ጋር በተያያዘ) በአሰሪው በኩል ያለ ህገወጥነትና፤ በመንግስት ደርጃ ደግሞ የባህረኞችን ጉዳይ የሚመለከተው መስሪያ ቤት በግልፅ አለመቀመጥ ወይም የተሰጠውን ሃላፊነት ጠንቅቆ ያለማወቅና ግድየለሽነት ነው።

 

አባል ሃገራት ሃላፊነት

እትዮጵያ (MLC) በአዋጅ ቁጥር 1063/2010 በ ህዳር 7/ 2010 አፅድቃለች። በኮንቬንሽኑ Article V(1) ላይ እንደተገለጸው International Maritime Convention (MLC) ፈርመው ያጸደቁ ሃገራት የሚጠበቅባቸው ሃላፊነት አለ። አንደኛው ሃላፊነት እያንዳንዱ አባል ሃገር መርከቦችንና ባህረኞችን በተመለከተ በ(MLC) የሚጠበቅበትን ቁርጠኝነት ለማሳካት ህግና ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ አለበት። ሁለተኛው ሃላፊነት Article V(7) ላይ እንደሰፈረው (MLC) ያላፀድቁ ሃገራት ከሌላው ሃገር በተለየ ምንም አስተያየት እንዳይደረግላቸው የደነግጋል። ይህም ማለት ለምሳሌ አንድ ባህረኛ (MLC) ባላፀደቀ ሃገር መርከብ ላይ ቢሰራና ያ መርከብ ወደ ሌላ ሃገር (MLC ያፀደቀ ሃገር) ቢሄድ፤ መርከቡም ሆነ መርከቡ ላይ የሚሰሩ ባህረኞች የተለየ አስተያየት ሳይደርግላቸው እንደማንኛውም (MLC) ሙሉ በሙሉ ማክበራቸውን በምርመራ ይረጋገጣል። ይህ ለባህረኛው መልካም ዜና ነው። ምክንያቱም የባህረኛው መብት መከበሩን የሚከታተሉት የሚሰራበት መርከብ ሃገር (flag state) ብቻ ሳይሆን መርከቧ የደረሰችበት ሃገር (port states) ሁሉ በ Port State Control (PSC) ትፈተሻለች። ባህረኛውም መብቱ ከተነካ በተለይ የአደጉት ሃገራት መርከቧ ስትደርስ ለ Port State Control (PSC) መርከቧ ትታገዳለች። ይህ ለባሀረኛው ትልቅ እፎይታ ሲሆን ለአጭበርባሪ መርከብ ባለቤቶች ራስ ምታት ነው።

ወደ ሃገራችን ስንመጣ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ (MLC) ብታፀድቅም፤ በሃገሪቷ ውስጥ ግን በግልጽ የተቀመጠ ህግ ከአዋጅ ቁጥር 1063/2010 ውጭ የምናውቀው የለም። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌላው በአዋጅ ቁጥር 1063/2010 መሰረት (MLC) ለማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው የመንግስት አካል የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ሲሆን፤ እንደኔ እይታ (MLC)ን የማስፈጸም ሃላፊነት ለማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን ቢሰጥ መልካም ነበር።፡ማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን ከባሀረኛው ጋር የጋራ ጥቅም ሲኖረው (በተለይ ከስልጠና እና ከህክምና ብቃት ጋር በተያያዘ) እንዲሁም የማሪታይም ዘርፍ የብዙ አመታት ልምድ ያለው መስሪያ ቤት ነው። ከሌሎች ሃገራት ልምድ እንደምናየውም የ (MLC) ማስፈጸም ሃላፊነት የተሰጠው ለማሪታይም ባለስልጣን ነው።

አስከአሁን ወደ ዋናው ጉዳይ አልገባንም። ከላይ እንደዘረዘርኩት፤ በአምስት ርዕሶች የተከፈሉት ዝርዝር ሁኔታዎችን ማየት ያስፈልጋል። እነዚህ አምስት ራዕሶች፤

 • Title 1: Minimum requirements for seafarers to work on a ship
 • Title 2: Conditions of employment
 • Title 3: Accommodation, recreational facilities, food and catering
 • Title 4: Health protection, medical care, welfare and social security protection
 • Title 5: Compliance and enforcement.

በሚቀጥለው እነዚህን አንድ ባንድ እየዘረዘርን እናያለን። እስከዛው ቸር እንሰንብት።

One thought on “የባህረኞች መብት – International Maritime Convention (MLC)

 1. ትልቁ ጥያቄ፡
  1, ያለስራ መቀመጥ ምን ይደረግ?
  2, ለምን ለአንድ ኤጀንት ብቻ ተፈቀደ?
  3, የክፍያ ጥያቄ
  3,1, የcost sharing ጉዳይ
  3,2, የደሞዝ

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s